የሳይፈን የመጨረሻ ተጠቃሚ የፍቃድ ስምምነት

ይህ ሶፍትዌር እና ማንኛውም ተዛማጅ አዕምሯዊ ንብረት ዋና ቢሮው በቶሮንቶ፣ ኦንታርዮ ካናዳ ያለው እና በኦንታሪዎ ኮርፖሬሽን የተመዘገበው የሳይፈን ኩባንያ ንብረት ነው።

የሳይፈን ስርአት “ሶፍትዌር” (የፕሮግራሙ ምንጨ ኮድ እና ከኮዱ የተቀዱ መተግበሪያዎች) እና “አገልግሎት” (ሁሉንም እንዲሰራ የሚያደርግ የደምበኛ እና የአገልጋይ ሶፍትዌር ስርአት ) ያካትታል።  የሳይፈን ሶፍትዌር እና ምንጨ ኮድ ነጻ እና ክፍተ ምንጭ እና በGNU አጠቃላይ የህዝብ ፈቃድ 3 መሰረት ፍቃድ ያላቸው ናቸው። የሳይፈን አገልግሎትን መጠቀም በዚህ ገጽ ላይ በተገለጸው ስምምነት ፍቃድ ያለው ነው።

የሳይፈን አገልገሎት በጥብቅ ለግለሰቦች እና ለግል ጥቅም ብቻ የታሰበ ነው። ሳይፈንን ለሌላ አላማ መጠቀመም ከፈለጉ ወይም ተጨማሪ መስፈርቶች ካሉዎት በክፍያ የንግድ አገልግሎት እንሰጣለን። ለበለጠ መረጃ በ sponsor@psiphon.ca ኢሜል ያድርጉልን።

የአጠቃቀም ስምምነቶች

የሳይፈን አገልግሎትን በሚጠቀሙበት ጊዜ ማንኛውንም አይነት የካናዳን ህግ ወይም ሌላ የሶስተኛ ወገን መብት በማይጥስ መልኩ ለመጠቀም ተስማምተው ነው።

የግል ወይም የተለየ ጥቅም

የሳይፈን አገልግሎትን መጠቀም የሚፈቀደው ብቸኛ ባልሆነ የግል ፍቃድ አማካኝነት ነው። ሳይፈንን ሲጠቀሙ አገልግሎቱን የሚጠቀሙት ለግል እደሆነ እና የንግድ ስራ እንዳልሆነ ተስማምተው ነው። የሳይፈንን አገልግሎት (እርስዎም ሆኑ ሌላ ሶስተኛ አካል) መከራየት፣ ማከራየት፣ ፍቃድ መስጠት፣ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለንግድ ስራ ማሰራጨት አይችሉም።

ስርጭት

በሳይፈን ኩባንያ የተፈጠሩ የሶፍትዌር ደንበኞች ብቻ የሰይፈን አገልግሎትን እንዲጠቀሙ ተፈቅዶላቸዋል። በሳይፈን አገልግሎትን ከሶስተኛ ወገን ደምበኛ ወይም መሳሪያ ጋር መጠቀም ወይም ማከፋፈል ይህንን ፈቃድ መጣስ ነው።

የተጠያቂነት ገደብ መግለጫ

The Psiphon service is provided “as is” and without warranty or expressed or implied liability of any kind. Psiphon disclaims all warranties and liabilities associated with the use of this service, including personal injury, or any incidental, special, indirect or consequential personal or commercial damages whatsoever, including loss of data and business interruption.

መቋረጥ፤ የአገልግሎት ስምምነት ጥሰቶች

ሳይፈን ይህንን ፈቃድ በፈለገ ሰአት፣ በማንኛውም ወይም ያለምንም ምክንያት፣ እና ያለ ምንም ቅጣት የማቋረጥ መብት ሙሉ በሙሉ አለው። የሳይፈንን አገልግሎትን ሲጠቀሙ የአገልግሎት ስምምነቶች እና የፈቃድ ስምምነቶችን በማይጥስ መልኩ እንደሚጠቀሙ ተስማምተው ነው።

እንደ ተጠቃሚ ማንኛውንም ወይም ሁሉንም የሳይፈን አገልግሎቶች መጠቀም በማቆም እና ከመሳሪያዎ ላይ የመተገበሪያውን ሁሉንም ሁኔታዎች በማጥፋት የመጠቀሚያ ፍቃዱን በፈለጉት ሰአት ማቋረጥ ይችላሉ።

የPsiCash አጠቃቀም

  1. If there is no PsiCash activity on your device for one year, then Psiphon reserves the right to cancel your PsiCash.
  2. If you lose track of your PsiCash, for example by losing your device, then you acknowledge that Psiphon will not be able to correct this mistake and restore your PsiCash.
  3. Psiphon reserves the right to change the rewards exchangeable for PsiCash at any time.