የPsiphon አጠቃቀም

Psiphon ለAndroid

በመጀመሪያ የPsiphon ለAndroid ቅዲዎ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት።

መጫንን ለማስጀመር የPsiphon APK ትይይዝን ከAndroid ኤፖስታ ተገልጋይ ላይ ወይም የድር መዳሰሻ ላይ ጠቅ ያድርጉ። (ስህተት ካገኙ የጎንዮሽ ጫኙን ማስቻል ሊያስፈልጎት ይችላል።)

የPsiphon መተግበሪያን በሚያስጀምሩበት ወቅት ከPsiphon ኔትወርክ ጋር መገናኘት በራሱ ይጀምራል።

Psiphon ለ Android ሁኔታ ፓነልን የሚያሳየው ቅጽበታዊ ገጽ እይታ
 • Psiphon እየሠራ ያለው በምናባዊ የግል አውታረ መረብ (ቪፒኤን) ወይም የመሣሪያ ሙሉ በሙሉ ሁነታ ነው። ሁሉም መተግበሪያዎች የሚዘዋወሩት በPsiphon አማካኝነት ነው።
 • የሁኔታ ትር ተመርጧል
 • Psiphonን በመሳሪያ ሙሉ በሙሉ ሁነታ መዘዋወሪያ ለማሰራት Android 4.0+ ወይም ሩትድ የሆነ መሳሪያ ሊኖርዎት ያስፈልጋል።

  ሩትድ ላልሆኑ የቆዩ የAndroid ስሪቶች ይህ አማራጭ አይገኝም ።
 • ግራጫ፡- በመገናኘት ላይ
  ቀይ፡- አልተገናኘም
  ሰማያዊ፡- ተገኛኝቷል
 • እየተጠቀሙ ያሉት የትኛውን የPsiphon ሥሪት እንደሆነ ያሳያል

Psiphon ለ Android (አንድሮይድ) ምዝግብ ፓነል የሚያሳይ ቅጽበታዊ የገጽ እይታ
 • የPsiphon እንቅስቃሴ መዝገብ

Psiphon ለAndroid ስታቲስቲክስ ፓኔል የሚያሳየው ቅጽበታዊ ገጽ እይታ
 • የግንኙነት ቆይታ
 • በPsiphon በኩል የተላከ ውሂብ
 • በPsiphon በኩል የደረሰ ውሂብ
 • በPsiphon በኩል ታምቆ የተላከ ውሂብ
 • በPsiphon በኩል ታምቆ የደረሰ ውሂብ

መተግበሪያው ከኔትወርኩ ጋር አንዴ ከተገናኘ አብሮ ገነብ የሆነውን የPsiphon መዳሰሻ ያስጀምራል። የAndroid Psiphon (Psiphon) ነባሪ የAndroid መዳሰሻን ወይም የሌሎች መተገበሪያዎች የኢንተርኔት ትራፊክን በራሱ አያዘዋውርም። በነባሪው በPsiphon ኔትወርክ ውስጥ የሚተላለፈው የPsiphon መዳሰሻ ብቻ ነው።

Psiphon ለAndroid የድር ማሰሻን የሚያሳይ ቅጽበታዊ ገጽ እይታ
 • Psiphon እየሠራ ነው
 • በተከፈቱ ትሮች መሃል ዝለል
 • አሁን ያለውን ትር ዝጋ
 • የአሁኑ ገጽ ላይ እልባት አድርግ
 • አዲስ ትር ክፈት